‘መጸለይን አስተምረን’ ወደ ሚለው ኮርስ እንኳን ደህና መጡ!
በዚህ አጭር ኮርስ ስለ ጸሎት፣ ጸሎት ምን እንደሆነ እና ለምንስ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ እንመለከታለን። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ባሉ ጥቂት ምሳሌዎች ላይም እንነጋገራለን። ትምህርቱ እግዚአብሔርን ወደሚያስደስት እና በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለዎትን እምነት ወደሚያጠናክር የጸሎት ህይወት ለመግባት የበለጠ ብርታት እንደሚሰጥዎት ተስፋ እናደርጋለን።
በጥናታችን ውስጥ አዲሱ አማርኛ መደበኛ ትርጉም የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም እንጠቀማለን።